Breaking News

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማቆያና ማገገሚያ ማዕከልን ጎበኙ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማቆያና ማገገሚያ ማዕከልን ጎበኙ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማቆያና ማገገሚያ ማዕከልን ጎበኙ

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ  በሱዳን ጉብኝታቸው ወቅት በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማቆያና ማገገሚያ ማዕከል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ጎብኝተዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሱዳን መጥተው ለተለያዩ የጤና ችግሮች የተጋለጡና መጠለያ የሌላቸው ዜጎቻችን እንዲሁም ወላጅ አልባ የሆኑ ሕጻናት ድጋፍ የሚያገኙበት በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ስር ያለውን ማቆያና ማገገሚያ ማዕከል (safe house) ነው ሚኒስትሩ የጎበኙት።

በማቆያ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻችን ስለቆይታቸውና ስለሚደረግላቸው ድጋፍም የማዕከሉን ተጠቃሚዎች አነጋግረዋል።

ሚኒስትሩ ማቆያ ማዕከሉ መንግስት በውጭ አገራት ለሚኖሩ ዜጎች መብቶችና ጥቅሞች መከበር የሰጠውን ትኩረት የሚያጎለብት በመሆኑ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡

ምንጭ ፤-የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃላ ቀባይ ጽ/ቤት

leave a reply